ኢትዮዽያ ፋብሪካ – ኢቲጂ
ፋብሪካችን
ኢትዮጵያ
አሻራዎን ያሳርፉ
የእኛ ተግባራት
የቡድን እንቅስቃሴዎች
የማህበረሰብ ተሳትፎ
ተቀላቀለን
እንታይ እዩ ኒሕካ? መስመር ኣውርዱልና።
ለማመልከትእባኮትን ሙሉ የስራ ልምድዎን ከሚጠበቁት ደሞዝ እና ከሚገኙበት ሁኔታ ጋር በመግለጽ ለዓብይ የሰው ሀብት አስተዳደር ክፍል በዚህ አያያዥ ይላኩ ( etg-recruit@talapparel.com)
ሁሉም መረጃዎች በከፍተኛ ሚስጥራዊነት ይስተናገዳሉ እና ለስራ ስምሪት ዓላማዎች ብቻ ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ድምጾች
ጌታሁን ሽብሩ
የታል ቤተሰብ አባል በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል:: ታል ለመላው ሰራተኞቹ እንደ ሁለተኛ ቤታችን ነው:: ከድርጅታችን ጋር ያለን ግንኙነት በስራ ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ተቀዳሚው አላማችን ዘለቄታዊ የሆነ አጋርነትን መፍጠርም ጭምር ነው:: እንደ ታል የሰራተኛ ማህበር ፕሬዝዳንትነቴ ታል የአለምን የፋሽን ኢንዱስትሪ ሲመራ ማየት ምኞቴ ነው::
ትዝታ ገነቱ
ለግል እና ለሙያ እድገት አበረታች ሁኔታ በመፍጠር በብዙዎች አድናቆትን ያተረፈው የታል አካል በመሆኔ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል። ታል ለስራ ምቹ የሆነ ተቋም ከመሆኑ ባሻገር በስሩ ያሉ ሰራተኞችም ተግባቢ ናቸው:: በዚህ ግሩም በሆነ የስራ ጉዞዬ ላይ ሙሉ አቅሜን ሳልሰስት እሰጣለሁ፤ የዚህ ጉዞ ተሳታፊ እንድሆን ለተሰጠኝ እድልም ከልብ የመነጨ ምስጋናዬን አቀርባለሁ::
መረሳ አብረሃ
ከሁሉም በላይ ለሰራተኞች የተሰጡ የእድገት እድሎችን አደንቃለሁ። እንደ ቀጣሪ፣ ታል ሰራተኞችን ማዳበር ለድርጅቱ ስኬት ቁልፍ እንደሆነ ያምናል፤ ሰራተኞቹም ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው ለማደግ እንዲችሉ የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት ለማረጋገጥ እወዳለው።
ሙሉጌታ አሸንጎ
የእስካሁኑ የታል የአይቲ ድጋፍ ቆይታዬ በስራዬ ብቻ ሳይሆን በግል ህይወቴም ውጤት-ተኮር አመለካከት እንዲኖረኝ አድርጎኛል። ከተለያየና በሙያ በዳበሩ ባለብዙ ባህል የስራ ማህበረሰብ ውስጥ መሆኔ በእጅጉ የምክሰኝ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ከዚህም በተጨማሪ የታል ለእያንዳዱ ሰራተኛ ያለው ቁርጠኛነቱ የታልን የራሱን ደረጃ ከፍ ያደረገና የራሴን መጻኢ የስራ እድገት ተስፋ እንድጥልበት ያደረገ ነው።
አዱኛ ተሾመ
ታልን በመቀላቀሌ እጅግ ደስተኛ ነኝ። በቁርጠኝነት ራሴን በማሳደግ የወደፊት ምኞቶቼን ወደ ተጨባጭ ስኬቶች እንድቀይር ጥሩ መድረክ ፈጥሮልኛል። የኢቲጂ ፈር ቀዳጅ ሰራተኛ እንደመሆኔ ለሰራተኞቻችን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ከሚጥሩ ባልደረቦቼ ጋር በጋራ በመሆን በቅጥር እና በሰራተኞች ግንኙነት ስራዎች ዙሪያ ፍትሃዊ እና ግልፅ አሰራርን ለማስፈን በትጋት እየሰራሁ እገኛለሁ::
ኩሳክ ኪትሌርባንቾንግ
ታል በተለያዩ የስራ መደቦች ላይ የመማርን እድል ይሰጣል:: መረጃ በተገቢው መንገድ ለሰራተኛ ያደርሳል:: እድገታችን የሚወሰነው በመማር አቅማችን ልክ ነው::